አምዶች

ስለ ኮሚሽኑ (About Us)

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የመንግሥታት ግንኙነት እና ከክልሉ ውጭ ያሉ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ኮሚሽን

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የመንግሥታት ግንኙነት እና ከክልሉ ውጭ ያሉ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ኮሚሽን ሀገራዊ እና ክልላዊ መስተጋብሮችን ለማቀናጀትና በብቃት ለመምራት የተቋቋመ የክልሉ መንግሥት አስፈጻሚ አካል ነው።

ተቋማዊ ሽግግርና ህጋዊ ማዕቀፍ

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የመንግስታት ግንኙነትን አስፈላጊነት በመረዳት የበይነ-መንግስታት ግንኙነቶች ቢሮ ከ2011 ዓ.ም ጀምሮ በማቋቋም ሲሰራ የቆየ ሲሆን የኢፌዲሪ መንግስት የመንግስታት ግንኙነት ሥርዓት መወሰኛ አዋጅ ቁጥር 1231/2013 በማውጣቱ ተቋሙ በዚሁ ሕግ መሠረት ሥራዎቹን ሲሰራ ቆይቷል።

ይህን አሠራር ይበልጥ ለማጠናከርና በላቀ ደረጃ ለማስቀጠል የክልሉ መንግሥት አዲስ አዋጅና ደንብ በማውጣት ተቋሙን ሙሉ ሥልጣንና ህጋዊ ሰውነት ሰጥቶ እንደገና አደራጅቶታል።

በዚህም መሠረት በተሻሻለው «የአስፈፃሚ አካላት ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 300/2017 አንቀጽ 51» እና «በክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 245/2018» መሠረት ኮሚሽኑ ራሱን የቻለ የክልሉ መንግሥት አስፈጻሚ አካል ሆኖ ተቋቁሟል።

ራዕይ (Vision)

በ2022 ለአማራ ብሔራዊ ክልል ዘላቂ ሰላምና ልማት ጉልህ አስተዋጽኦ የሚያበረክት ውጤታማ የመንግስታት ግንኙነትና ትብብር፣ የባለድርሻና አጋር አካላት ተሳትፎ እና የህዝቦች አብሮነት ጎልብቶ ማየት።

ተልዕኮ (Mission)

የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ከፌደራል መንግስት፣ ከክልል መንግስታት እና ከክልሉ ውጭ ከሚገኙ የባለድርሻና አጋር አካላት ጋር ያለውን ግንኙነትና ተሳትፎ በብቃት በማስተባበርና በማቀናጀት፣ የክልሉን ህዝብና መንግስት መልካም ገፅታ ከክልሉ ውጭ በማስተዋወቅና የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቶችን የሚያጠናክሩ ተግባራትን በማከናዎን ለክልሉ ዘላቂ ሰላምና ልማት አስተዋጽኦ ማበርከት።