የኮሚሽኑ ራዕይ፣ ተልዕኮ እና ስትራቴጂያዊ ጉዳዮች፣አላማዎችና ግቦች
የኮሚሽኑ ርእይ/ Vision
በ2022 ለአማራ ብሔራዊ ክልል ዘላቂ ሰላምና ልማት ጉልህ አስተዋጽኦ የሚያበረክት ውጤታማ የመንግስታት ግንኙነትና ትብብር፣ የባለድርሻና አጋር አካላት ተሳትፎ እና የህዝቦች አብሮነት ጎልብቶ ማየት
የኮሚሽኑ ተልዕኮ /Mission/
የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ከፌደራል መንግስት፣ ከክልል መንግስታት እና ከክልሉ ውጭ ከሚገኙ የባለድርሻና አጋር አካላት ጋር ያለውን ግንኙነትና ተሳትፎ በብቃት በማስተባበርና በማቀናጀት፣ የክልሉን ህዝብና መንግስት መልካም ገፅታ ከክልሉ ውጭ በማስተዋወቅና የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቶችን የሚያጠናክሩ ተግባራትን በማከናዎን ለክልሉ ዘላቂ ሰላምና ልማት አስተዋጽኦ ማበርከት
እሴቶች
1. ያለ ክንፍ መብረር ያለ ሙያ መክበር አይቻልምና በሙያ ብቃት እንክበር፤
2. መታዘዝ ከመስዋዕትነት ይበልጣልና ምርጫችን አገልጋይነት ነው፤
3. የሰው ወርቅ አያደምቅምና በራሳችን ባህል እንደምቃለን፤ እንጠበቃለን፤
4. አበው በህግ አምላክ ብለው እንደተገዙለት እኛም ለህግ እንገዛለን፤
5. ከባህር የወጣ ዓሳ ላለመሆን ሕዝባዊ ወገንተኝነትን አጥብቀናል፤
6. ከመቃብር በላይ ስም ይቆማልና አርበኝነት መለያችን ነው፤
7. ብልህ የዓመቱን፣ ሞኝ የእለቱን ነውና እንደ ብልሆች ሀብትን በአግባቡ ቆጥበን እንጠቀማለን፤
8. መልካም ሃሳብ ወንዝ ያሻግራልና ልዕለ ሐሳብ ይገዛናል፤
9. መድረሻውን ያላወቀ የትም ይገኛልና ትኩረታችን ለግቦቻችን ይሁን ብለናል፤
10. ልዩነታችን ውበት ነውና ብዝሐነት ተቀብለናል፤
11. ቋጠሮ መፍታት ከውሉ እንዲሉ ምርምርና ፈጠራን ለችግራችን መፍቻ አድርገናል፤
12. ድር ቢያብር አንበሳ ያሥር ነውና ቅንጅታዊ አሠራር እሴታችን ነው፤
13. አለባብሰው ቢያርሱ በአረም ይመለሱ በመሆኑ ግልፅነትና ተጠያቂነት እሴታችን ነው፡፡