አምዶች
የቅርብ ዜና
• በኮሚሽኑ ስትራቴጂካዊ ጉዳዮችና ከባለሙያዎች በሚጠበቁ ሙያዊ ሃላፊነቶች ላይ ያተኮረ የኢንዳክሽን ስልጠና ተሰጠ • በክልሉ መንግሥት አዲሱ የግዥ አዋጅና አፈጻጸም መመሪያ ላይ ለስራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ተጠናቀቀ • ኮሚሽኑ ከኢንዱስትሪ ፕሮጀክቶች አገልግሎት ከፍተኛ አመራሮች ጋር በትብብር መሥራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ መከረ • በአዲሱ የክልሉ የመንግሥት ግዥ አዋጅና የአፈጻጸም መመሪያ ላይ ለስራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ስልጠና እየተሰጠ ነው። • ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 01/2019 • "በተቋማት መካከል የተጠናከረ ግንኙነት እንዲኖር እሰራለሁ" የአማራ ክልል የመንግስታት ግንኙነትና ከክልሉ ውጭ ያሉ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ኮሚሽን • የኮሚሽኑ የ5 ዓመት ስትራቴጂና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ የውይይት መድረክ ተካሄደ • የኮሚሽኑ ራዕይ፣ ተልዕኮ እና ስትራቴጂያዊ ጉዳዮች፣አላማዎችና ግቦች • የኮሚሽነሩ መልዕክት • በኮሚሽኑ ስትራቴጂካዊ ጉዳዮችና ከባለሙያዎች በሚጠበቁ ሙያዊ ሃላፊነቶች ላይ ያተኮረ የኢንዳክሽን ስልጠና ተሰጠ • በክልሉ መንግሥት አዲሱ የግዥ አዋጅና አፈጻጸም መመሪያ ላይ ለስራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ተጠናቀቀ • ኮሚሽኑ ከኢንዱስትሪ ፕሮጀክቶች አገልግሎት ከፍተኛ አመራሮች ጋር በትብብር መሥራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ መከረ • በአዲሱ የክልሉ የመንግሥት ግዥ አዋጅና የአፈጻጸም መመሪያ ላይ ለስራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ስልጠና እየተሰጠ ነው። • ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 01/2019 • "በተቋማት መካከል የተጠናከረ ግንኙነት እንዲኖር እሰራለሁ" የአማራ ክልል የመንግስታት ግንኙነትና ከክልሉ ውጭ ያሉ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ኮሚሽን • የኮሚሽኑ የ5 ዓመት ስትራቴጂና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ የውይይት መድረክ ተካሄደ • የኮሚሽኑ ራዕይ፣ ተልዕኮ እና ስትራቴጂያዊ ጉዳዮች፣አላማዎችና ግቦች • የኮሚሽነሩ መልዕክት
የሚዲያ ማዕከል / ቅርብ ጊዜ ዜናዎች

የኮሚሽኑ የ5 ዓመት ስትራቴጂና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ የውይይት መድረክ ተካሄደ

በዘላለም ግርማ | October 7, 2026

አመግ፡ መስከረም 14/2019፡- የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የመንግሥታት ግንኙነትና ከክልሉ ውጭ ያሉ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ኮሚሽን የ5 ዓመት ስትራቴጂ እና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ ያተኮረ የባለድርሻና አጋር አካላት የውይይት መድረክ ዛሬ መስከረም 14 ቀን 2019 ዓም ተካሂዷል። 

በመድረኩ የኮሚሽኑን የ5 ዓመት ስትራቴጂና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ያቀረቡት የአማራ ክልል የመንግሥታት ግንኙነትና ከክልሉ ውጭ ያሉ ጉዳዮች ኮሚሽን ኮሚሽነር ክቡር ዶ/ር ደስታ ተስፋው እንደተናገሩት የክልሉ መንግሥት ከፌደራል እና ከሌሎች ክልሎች ጋር ሰላምና ልማትን ለማጎልበት የ25 ዓመት የአሻጋሪ ዕድገትና የዘላቂ ልማት ፍኖተ-ካርታ (2018-2042) ተዘጋጅቶ የመጀመሪያው የ5 ዓመት ስትራቴጂክ ዕቅድ ተግባራዊ በመሆን ላይ ይገኛል። 

ኮሚሽኑ ከተቋቋመበት ዋና ዓላማዎች መካከል የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቶችን ማጠናከር፣ ብሔራዊ ገዥ ትርክትን ማስረጽ፣ እና የክልሉን ሕዝብና መንግሥት መልካም ገጽታ ከክልሉ ውጭ በማስተዋወቅ ረገድ አስተዋጽኦ ማበርከት መሆናቸውን ኮሚሽነሩ ጠቅሰዋል።

በውይይት መድረኩ ላይ የውስጥ ጥንካሬዎች፣ ድክመቶች፣ መልካም ዕድሎች እና ስጋቶች ቀርበዋል። 

ኮሚሽነር ክቡር ዶ/ር ደስታ አክለው ሲገልፁ የክልሉን ሁለንተናዊ ሰላምና ልማት ለማረጋገጥ ሁሉም ባለድርሻ አካላትና አጋር ድርጅቶች የተቀናጀ ርብርብ ማድረግ እንደሚገባቸው አጽንኦት ሰጥተዋል። 

በመድረኩ የተገኙ ባለድርሻ እና አጋር አካላት ከኮሚሽኑ ጋር በጋራ በሚሠሯቸው ሥራዎች ላይ ያላቸውን ገንቢ አስተያየቶች አጋርተዋል፤ አብሮነቱን ይበልጥ ለማጠናከርም የጋራ ዕቅድ አውጥተው በቅንጅት መሥራት እንደሚፈልጉ ገልጸዋል።

ተጨማሪ ዜናዎችን ያንብቡ

ማህበራዊ - ሚዲያ

የአማራ የመንግስታት ግንኙነት ዘገባዎችን በሁሉም ማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች ይከታተሉ