አምዶች
የቅርብ ዜና
• በኮሚሽኑ ስትራቴጂካዊ ጉዳዮችና ከባለሙያዎች በሚጠበቁ ሙያዊ ሃላፊነቶች ላይ ያተኮረ የኢንዳክሽን ስልጠና ተሰጠ • በክልሉ መንግሥት አዲሱ የግዥ አዋጅና አፈጻጸም መመሪያ ላይ ለስራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ተጠናቀቀ • ኮሚሽኑ ከኢንዱስትሪ ፕሮጀክቶች አገልግሎት ከፍተኛ አመራሮች ጋር በትብብር መሥራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ መከረ • በአዲሱ የክልሉ የመንግሥት ግዥ አዋጅና የአፈጻጸም መመሪያ ላይ ለስራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ስልጠና እየተሰጠ ነው። • ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 01/2019 • "በተቋማት መካከል የተጠናከረ ግንኙነት እንዲኖር እሰራለሁ" የአማራ ክልል የመንግስታት ግንኙነትና ከክልሉ ውጭ ያሉ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ኮሚሽን • የኮሚሽኑ የ5 ዓመት ስትራቴጂና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ የውይይት መድረክ ተካሄደ • የኮሚሽኑ ራዕይ፣ ተልዕኮ እና ስትራቴጂያዊ ጉዳዮች፣አላማዎችና ግቦች • የኮሚሽነሩ መልዕክት • በኮሚሽኑ ስትራቴጂካዊ ጉዳዮችና ከባለሙያዎች በሚጠበቁ ሙያዊ ሃላፊነቶች ላይ ያተኮረ የኢንዳክሽን ስልጠና ተሰጠ • በክልሉ መንግሥት አዲሱ የግዥ አዋጅና አፈጻጸም መመሪያ ላይ ለስራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ተጠናቀቀ • ኮሚሽኑ ከኢንዱስትሪ ፕሮጀክቶች አገልግሎት ከፍተኛ አመራሮች ጋር በትብብር መሥራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ መከረ • በአዲሱ የክልሉ የመንግሥት ግዥ አዋጅና የአፈጻጸም መመሪያ ላይ ለስራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ስልጠና እየተሰጠ ነው። • ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 01/2019 • "በተቋማት መካከል የተጠናከረ ግንኙነት እንዲኖር እሰራለሁ" የአማራ ክልል የመንግስታት ግንኙነትና ከክልሉ ውጭ ያሉ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ኮሚሽን • የኮሚሽኑ የ5 ዓመት ስትራቴጂና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ የውይይት መድረክ ተካሄደ • የኮሚሽኑ ራዕይ፣ ተልዕኮ እና ስትራቴጂያዊ ጉዳዮች፣አላማዎችና ግቦች • የኮሚሽነሩ መልዕክት
ስለ እኛ / ራዕይ እና ተልዕኮ

የኮሚሽኑ ራዕይ፣ ተልዕኮ እና ስትራቴጂያዊ ጉዳዮች፣አላማዎችና ግቦች

October 7, 2026

የኮሚሽኑ ርእይ/ Vision

በ2022 ለአማራ ብሔራዊ ክልል ዘላቂ ሰላምና ልማት ጉልህ አስተዋጽኦ የሚያበረክት ውጤታማ የመንግስታት ግንኙነትና ትብብር፣ የባለድርሻና አጋር አካላት ተሳትፎ እና የህዝቦች አብሮነት ጎልብቶ ማየት

የኮሚሽኑ ተልዕኮ /Mission/

የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ከፌደራል መንግስት፣ ከክልል መንግስታት እና ከክልሉ ውጭ ከሚገኙ የባለድርሻና አጋር አካላት ጋር ያለውን ግንኙነትና ተሳትፎ በብቃት በማስተባበርና በማቀናጀት፣ የክልሉን ህዝብና መንግስት መልካም ገፅታ ከክልሉ ውጭ በማስተዋወቅና የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቶችን የሚያጠናክሩ ተግባራትን በማከናዎን ለክልሉ ዘላቂ ሰላምና ልማት አስተዋጽኦ ማበርከት

እሴቶች

1.  ያለ ክንፍ መብረር ያለ ሙያ መክበር አይቻልምና በሙያ ብቃት እንክበር፤

2.  መታዘዝ ከመስዋዕትነት ይበልጣልና ምርጫችን አገልጋይነት ነው፤

3.  የሰው ወርቅ አያደምቅምና በራሳችን ባህል እንደምቃለን፤ እንጠበቃለን፤

4.  አበው በህግ አምላክ ብለው እንደተገዙለት እኛም ለህግ እንገዛለን፤

5.  ከባህር የወጣ ዓሳ ላለመሆን ሕዝባዊ ወገንተኝነትን አጥብቀናል፤

6.  ከመቃብር በላይ ስም ይቆማልና አርበኝነት መለያችን ነው፤

7.  ብልህ የዓመቱን፣ ሞኝ የእለቱን ነውና እንደ ብልሆች ሀብትን በአግባቡ ቆጥበን እንጠቀማለን፤

8.  መልካም ሃሳብ ወንዝ ያሻግራልና ልዕለ ሐሳብ ይገዛናል፤

9.  መድረሻውን ያላወቀ የትም ይገኛልና ትኩረታችን ለግቦቻችን ይሁን ብለናል፤

10. ልዩነታችን ውበት ነውና ብዝሐነት ተቀብለናል፤

11. ቋጠሮ መፍታት ከውሉ እንዲሉ ምርምርና ፈጠራን ለችግራችን መፍቻ አድርገናል፤

12. ድር ቢያብር አንበሳ ያሥር ነውና ቅንጅታዊ አሠራር እሴታችን ነው፤

13. አለባብሰው ቢያርሱ በአረም ይመለሱ በመሆኑ ግልፅነትና ተጠያቂነት እሴታችን ነው፡፡

ተጨማሪ ዜናዎችን ያንብቡ

ማህበራዊ - ሚዲያ

የአማራ የመንግስታት ግንኙነት ዘገባዎችን በሁሉም ማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች ይከታተሉ