አምዶች
የቅርብ ዜና
• በኮሚሽኑ ስትራቴጂካዊ ጉዳዮችና ከባለሙያዎች በሚጠበቁ ሙያዊ ሃላፊነቶች ላይ ያተኮረ የኢንዳክሽን ስልጠና ተሰጠ • በክልሉ መንግሥት አዲሱ የግዥ አዋጅና አፈጻጸም መመሪያ ላይ ለስራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ተጠናቀቀ • ኮሚሽኑ ከኢንዱስትሪ ፕሮጀክቶች አገልግሎት ከፍተኛ አመራሮች ጋር በትብብር መሥራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ መከረ • በአዲሱ የክልሉ የመንግሥት ግዥ አዋጅና የአፈጻጸም መመሪያ ላይ ለስራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ስልጠና እየተሰጠ ነው። • ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 01/2019 • "በተቋማት መካከል የተጠናከረ ግንኙነት እንዲኖር እሰራለሁ" የአማራ ክልል የመንግስታት ግንኙነትና ከክልሉ ውጭ ያሉ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ኮሚሽን • የኮሚሽኑ የ5 ዓመት ስትራቴጂና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ የውይይት መድረክ ተካሄደ • የኮሚሽኑ ራዕይ፣ ተልዕኮ እና ስትራቴጂያዊ ጉዳዮች፣አላማዎችና ግቦች • የኮሚሽነሩ መልዕክት • በኮሚሽኑ ስትራቴጂካዊ ጉዳዮችና ከባለሙያዎች በሚጠበቁ ሙያዊ ሃላፊነቶች ላይ ያተኮረ የኢንዳክሽን ስልጠና ተሰጠ • በክልሉ መንግሥት አዲሱ የግዥ አዋጅና አፈጻጸም መመሪያ ላይ ለስራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ተጠናቀቀ • ኮሚሽኑ ከኢንዱስትሪ ፕሮጀክቶች አገልግሎት ከፍተኛ አመራሮች ጋር በትብብር መሥራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ መከረ • በአዲሱ የክልሉ የመንግሥት ግዥ አዋጅና የአፈጻጸም መመሪያ ላይ ለስራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ስልጠና እየተሰጠ ነው። • ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 01/2019 • "በተቋማት መካከል የተጠናከረ ግንኙነት እንዲኖር እሰራለሁ" የአማራ ክልል የመንግስታት ግንኙነትና ከክልሉ ውጭ ያሉ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ኮሚሽን • የኮሚሽኑ የ5 ዓመት ስትራቴጂና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ የውይይት መድረክ ተካሄደ • የኮሚሽኑ ራዕይ፣ ተልዕኮ እና ስትራቴጂያዊ ጉዳዮች፣አላማዎችና ግቦች • የኮሚሽነሩ መልዕክት
የሚዲያ ማዕከል / ቅርብ ጊዜ ዜናዎች

በክልሉ መንግሥት አዲሱ የግዥ አዋጅና አፈጻጸም መመሪያ ላይ ለስራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ተጠናቀቀ

በዘላለም ግርማ | November 16, 2026

ሕዳር 4/2019፡- በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የመንግሥታት ግንኙነትና ከክልሉ ውጭ ያሉ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ኮሚሽን፣ በክልሉ መንግሥት በወጣው አዲሱ የግዥ አዋጅና አፈጻጸም መመሪያ ላይ ለስራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ለተከታታይ ሶስት ቀናት ሲሰጥ የቆየው ስልጠና በስኬት ተጠናቋል።

በሥልጠናው ማጠቃለያ ላይ የተገኙት የአማራ ክልል የመንግሥታት ግንኙነትና ከክልሉ ውጭ ያሉ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ኮሚሽን ኮሚሽነር ክቡር ዶ/ር ደስታ ተስፋው እንደገለጹት፤ ኮሚሽኑ የተጣለበትን ከፍተኛ ኃላፊነት በአግባቡ ለመወጣት ግልጽና ቀልጣፋ የግዥ ሥርዓት መዘርጋት ወሳኝ ነው። ይህ መድረክም የመንግሥት በጀት ለታለመለት ዓላማ ብቻ እንዲውልና ተቋማዊ አፈጻጸምን ለማሳደግ በክልሉ የግዥ ሕጎች ላይ የተሟላ መግባባት ለመፍጠር ያስቻለ መሆኑን አስገንዝበዋል።
ኮሚሽነሩ አክለውም ተሳታፊዎች በነበራቸው የሶስት ቀናት ቆይታ በክልሉ መንግሥት ተሻሽሎ የወጣውን አዲስ የግዢ አዋጅና የአሰራር መመሪያ በተሻለ ሁኔታ በመረዳትና በመገንዘብ፣ በቀጣይ የሚፈጸሙ የግዢ ሂደቶችን በብቃትና በኃላፊነት ለመወጣት የሚያስችላቸውን በቂ ዕውቀትና ተግባራዊ ክህሎት መጨበጣቸውን ተናግረዋል።

የኮሚሽኑ የግዥ፣ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክተር አቶ ዘላለም ጥላሁን በበኩላቸው፤ ባለፉት ሶስት ቀናት በሰጡት ስልጠና የክልሉን አዲስ የግዥ አዋጁን እና መመሪያ ቁጥር 144/2018ን መሠረታዊ ጽንሰ-ሐሳቦች፣ የግዥ ዘዴዎችን፣ የሰነድ አያያዝ ስርዓትን እንዲሁም በስራ ሂደት የሚያጋጥሙ ችግሮችን የመፍቻ አቅጣጫዎች በዝርዝር መዳሰሳቸውን ገልጸዋል። ይህም በግዥ ስራ ላይ የተሰማሩ ባለሙያዎችና አመራሮች መመሪያውን በተሻለ ሁኔታ ተረድተው በተግባር እንዲተረጉሙት ትልቅ አቅም እንደፈጠረላቸው አስረድተዋል።

ተጨማሪ ዜናዎችን ያንብቡ

ማህበራዊ - ሚዲያ

የአማራ የመንግስታት ግንኙነት ዘገባዎችን በሁሉም ማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች ይከታተሉ