አምዶች
የቅርብ ዜና
• በኮሚሽኑ ስትራቴጂካዊ ጉዳዮችና ከባለሙያዎች በሚጠበቁ ሙያዊ ሃላፊነቶች ላይ ያተኮረ የኢንዳክሽን ስልጠና ተሰጠ • በክልሉ መንግሥት አዲሱ የግዥ አዋጅና አፈጻጸም መመሪያ ላይ ለስራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ተጠናቀቀ • ኮሚሽኑ ከኢንዱስትሪ ፕሮጀክቶች አገልግሎት ከፍተኛ አመራሮች ጋር በትብብር መሥራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ መከረ • በአዲሱ የክልሉ የመንግሥት ግዥ አዋጅና የአፈጻጸም መመሪያ ላይ ለስራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ስልጠና እየተሰጠ ነው። • ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 01/2019 • "በተቋማት መካከል የተጠናከረ ግንኙነት እንዲኖር እሰራለሁ" የአማራ ክልል የመንግስታት ግንኙነትና ከክልሉ ውጭ ያሉ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ኮሚሽን • የኮሚሽኑ የ5 ዓመት ስትራቴጂና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ የውይይት መድረክ ተካሄደ • የኮሚሽኑ ራዕይ፣ ተልዕኮ እና ስትራቴጂያዊ ጉዳዮች፣አላማዎችና ግቦች • የኮሚሽነሩ መልዕክት • በኮሚሽኑ ስትራቴጂካዊ ጉዳዮችና ከባለሙያዎች በሚጠበቁ ሙያዊ ሃላፊነቶች ላይ ያተኮረ የኢንዳክሽን ስልጠና ተሰጠ • በክልሉ መንግሥት አዲሱ የግዥ አዋጅና አፈጻጸም መመሪያ ላይ ለስራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ተጠናቀቀ • ኮሚሽኑ ከኢንዱስትሪ ፕሮጀክቶች አገልግሎት ከፍተኛ አመራሮች ጋር በትብብር መሥራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ መከረ • በአዲሱ የክልሉ የመንግሥት ግዥ አዋጅና የአፈጻጸም መመሪያ ላይ ለስራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ስልጠና እየተሰጠ ነው። • ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 01/2019 • "በተቋማት መካከል የተጠናከረ ግንኙነት እንዲኖር እሰራለሁ" የአማራ ክልል የመንግስታት ግንኙነትና ከክልሉ ውጭ ያሉ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ኮሚሽን • የኮሚሽኑ የ5 ዓመት ስትራቴጂና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ የውይይት መድረክ ተካሄደ • የኮሚሽኑ ራዕይ፣ ተልዕኮ እና ስትራቴጂያዊ ጉዳዮች፣አላማዎችና ግቦች • የኮሚሽነሩ መልዕክት
የሚዲያ ማዕከል / ቅርብ ጊዜ ዜናዎች

ኮሚሽኑ ከኢንዱስትሪ ፕሮጀክቶች አገልግሎት ከፍተኛ አመራሮች ጋር በትብብር መሥራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ መከረ

በዘላለም ግርማ | November 12, 2026

አዲስ አበባ፤ ህዳር 3 ቀን 2019 ዓ.ም. — የአማራ ክልል የመንግሥታት ግንኙነትና ከክልሉ ውጭ ያሉ ጉዳዮች ማስተባባሪያ ኮሚሽን ከኢንዱስትሪ ፕሮጀክቶች አገልግሎት (IPS) ማኔጅመንት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጋር በትብብር መሥራት በሚቻልባቸው ዘርፎች ዙሪያ ዛሬ ህዳር 3 ቀን 2019 ዓ.ም የፊት ለፊት ውይይት አካሂዷል።

በውይይቱ ወቅት የአማራ ክልል የመንግስታት ግንኙነትና ከክልሉ ውጭ ያሉ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ኮሚሽን ኮሚሽነር ክቡር ዶ/ር ደስታ ተስፋው ኮሚሽኑ የተቋቋመበትን ዓላማዎች፣ ሥልጣንና ተግባራት፣ የክልሉን የ25 ዓመት የአሸጋሪ እድገትና የዘላቂ ልማት ፍኖተ-ካርታ እንዲሁም የ5 ዓመት ስትራቴጂክ ዕቅድ አቅርበዋል።

ክቡር ዶ/ር ደስታ አክለውም፣ ኮሚሽኑ የተቋቋመበት ዋና ምክንያት ከክልሉ ውጭ ያሉ ባለድርሻ አካላት ከክልሉ መንግሥት ጋር ያላቸውን ግንኙነት ማቀናጀትና ማሳለጥ መሆኑን ገልጸዋል።

የክልሉን የ25 ዓመት ፍኖተ-ካርታ በስኬት ተግባራዊ ለማድረግ እና የማስፈጸም ክፍተቶችን ለመሙላት የባለድርሻ አካላት ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን የጠቆሙት ኮሚሽነሩ፤ የኢንዱስትሪ ፕሮጀክቶች አገልግሎት ያለውን የካበተ ልምድ በመጠቀም ግንኙነቱን ማጠናከርና ተጨባጭ ሥራዎችን አቅዶ ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባ አሳስበዋል። የዛሬው ውይይትም ለወደፊቱ የጋራ ግንኙነት ጠንካራ መሠረት የሚጥል መሆኑን ተናግረዋል።

የኢንዱስትሪ ፕሮጀክቶች አገልግሎት (IPS) ከኮሚሽኑ ጋር በጋራ ሊሠራባቸው በሚችሉ የትብብር ማዕቀፎች እና የጋራ የሥራ መስኮች ላይ ሰፊ ገለፃ ቀርቧል።

በውይይቱ ወቅት የአገልግሎቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ሽፈራው ሰለሞን ሲያብራሩ፣ ተቋማቸው ባለፉት 40 ዓመታት በሀገሪቱ የሚገኙ ትልልቅ ተቋማትን የአዋጭነት ጥናት በመሥራት ወደ ትርፋማነት ለመመለስ በትኩረት እየሠራ የሚገኝ አንጋፋ ተቋም መሆኑን ገልጸዋል።

ዋና ሥራ አስኪያጁ አክለውም፤ አገልግሎቱ አዳዲስና ችግር ፈቺ የሆኑ የማማከርና የሥልጠና አገልግሎቶችን ለመስጠት ዝግጁ መሆኑንም አመልክተዋል።

በውይይቱ ማጠቃለያም ሁለቱ ተቋማት የቀረቡትን የትብብር መስኮች ወደ ተግባር ለመቀየር የሚያስችል የጋራ ዕቅድ በማዘጋጀት ግንኙነታቸውን ይበልጥ አጠናክረው ለመቀጠል ተስማምተዋል።

ተጨማሪ ዜናዎችን ያንብቡ

ማህበራዊ - ሚዲያ

የአማራ የመንግስታት ግንኙነት ዘገባዎችን በሁሉም ማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች ይከታተሉ