አምዶች
የቅርብ ዜና
• በኮሚሽኑ ስትራቴጂካዊ ጉዳዮችና ከባለሙያዎች በሚጠበቁ ሙያዊ ሃላፊነቶች ላይ ያተኮረ የኢንዳክሽን ስልጠና ተሰጠ • በክልሉ መንግሥት አዲሱ የግዥ አዋጅና አፈጻጸም መመሪያ ላይ ለስራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ተጠናቀቀ • ኮሚሽኑ ከኢንዱስትሪ ፕሮጀክቶች አገልግሎት ከፍተኛ አመራሮች ጋር በትብብር መሥራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ መከረ • በአዲሱ የክልሉ የመንግሥት ግዥ አዋጅና የአፈጻጸም መመሪያ ላይ ለስራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ስልጠና እየተሰጠ ነው። • ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 01/2019 • "በተቋማት መካከል የተጠናከረ ግንኙነት እንዲኖር እሰራለሁ" የአማራ ክልል የመንግስታት ግንኙነትና ከክልሉ ውጭ ያሉ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ኮሚሽን • የኮሚሽኑ የ5 ዓመት ስትራቴጂና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ የውይይት መድረክ ተካሄደ • የኮሚሽኑ ራዕይ፣ ተልዕኮ እና ስትራቴጂያዊ ጉዳዮች፣አላማዎችና ግቦች • የኮሚሽነሩ መልዕክት • በኮሚሽኑ ስትራቴጂካዊ ጉዳዮችና ከባለሙያዎች በሚጠበቁ ሙያዊ ሃላፊነቶች ላይ ያተኮረ የኢንዳክሽን ስልጠና ተሰጠ • በክልሉ መንግሥት አዲሱ የግዥ አዋጅና አፈጻጸም መመሪያ ላይ ለስራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ተጠናቀቀ • ኮሚሽኑ ከኢንዱስትሪ ፕሮጀክቶች አገልግሎት ከፍተኛ አመራሮች ጋር በትብብር መሥራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ መከረ • በአዲሱ የክልሉ የመንግሥት ግዥ አዋጅና የአፈጻጸም መመሪያ ላይ ለስራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ስልጠና እየተሰጠ ነው። • ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 01/2019 • "በተቋማት መካከል የተጠናከረ ግንኙነት እንዲኖር እሰራለሁ" የአማራ ክልል የመንግስታት ግንኙነትና ከክልሉ ውጭ ያሉ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ኮሚሽን • የኮሚሽኑ የ5 ዓመት ስትራቴጂና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ የውይይት መድረክ ተካሄደ • የኮሚሽኑ ራዕይ፣ ተልዕኮ እና ስትራቴጂያዊ ጉዳዮች፣አላማዎችና ግቦች • የኮሚሽነሩ መልዕክት
የሚዲያ ማዕከል / ቅርብ ጊዜ ዜናዎች

በአዲሱ የክልሉ የመንግሥት ግዥ አዋጅና የአፈጻጸም መመሪያ ላይ ለስራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ስልጠና እየተሰጠ ነው።

በዘላለም ግርማ | November 11, 2026
ሕዳር 2/2019፡- በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የመንግሥታት ግንኙነትና ከክልሉ ውጭ ያሉ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ኮሚሽን፣ በአዲሱ የክልሉ መንግሥት ግዥ አዋጅና አፈጻጸም መመሪያ ላይ ለስራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ለሶስት ቀናት የሚቆይ ስልጠና መስጠት ጀምሯል።
 
በሥልጠና መርሃ ግብሩ መክፈቻ ላይ ንግግር ያደረጉት በአማራ ክልል የመንግሥታት ግንኙነትና ከክልሉ ውጪ ያሉ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ኮሚሽን ኮሚሽነር ክቡር ዶ/ር ደስታ ተስፋው እንደገለፁት ስልጠናው ኮሚሽኑ የተሰጠውን ተግባርና ኃላፊነት በብቃት ለመወጣት የሚያስፈልጉ ግብአቶችን ለማሟላትና የተመደበለትን በጀት ለታለመለት አላማ እንዲውል ለማድረግና በውጤታማነት ለመጠቀም በክልሉ የወጣውን የግዥ አዋጅና አሰራር ላይ ተገቢውን ግንዛቤ ለማስጨበጥ ያለመ መሆኑን ገልፀዋል።
ኮሚሽነሩ አክለውም ተሳታፊዎች በዚህ የሶስት ቀናት ቆይታቸው አዲሱን የመንግሥት ግዢ አዋጅና የአሰራር መመሪያ በተሻለ ሁኔታ በመረዳትና በመገንዘብ፣ በቀጣይ የሚፈጸሙ የግዢ ሂደቶችን በብቃት ለመወጣት የሚያስችላቸውን በቂ ዕውቀትና ተግባራዊ ክህሎት እንደሚጨብጡ ይጠበቃል ብለዋል።
የኮሚሽኑ የግዥ፣ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክተር አቶ ዘላለም ጥላሁን በበኩላቸው የሥልጠናው መሠረታዊ ዓላማና ፋይዳ በግዥ ኮሚቴ ሥራ ላይ የተሰማሩ ሠራተኞችን እና በሥራ ባህሪያቸው ከግዥ ጋር የሚገናኙ አመራሮችን አዲስ የወጣውን የክልሉን የመንግሥት ግዥ አፈጻጸም አዋጅና መመሪያ ቁጥር 144/2018 በሥራ ላይ ለማዋል የሚያስችል ከፍተኛ ጠቃሜታ ያለው መሆኑን ገልጸዋል።

ተጨማሪ ዜናዎችን ያንብቡ

ማህበራዊ - ሚዲያ

የአማራ የመንግስታት ግንኙነት ዘገባዎችን በሁሉም ማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች ይከታተሉ