አምዶች
የቅርብ ዜና
• በኮሚሽኑ ስትራቴጂካዊ ጉዳዮችና ከባለሙያዎች በሚጠበቁ ሙያዊ ሃላፊነቶች ላይ ያተኮረ የኢንዳክሽን ስልጠና ተሰጠ • በክልሉ መንግሥት አዲሱ የግዥ አዋጅና አፈጻጸም መመሪያ ላይ ለስራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ተጠናቀቀ • ኮሚሽኑ ከኢንዱስትሪ ፕሮጀክቶች አገልግሎት ከፍተኛ አመራሮች ጋር በትብብር መሥራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ መከረ • በአዲሱ የክልሉ የመንግሥት ግዥ አዋጅና የአፈጻጸም መመሪያ ላይ ለስራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ስልጠና እየተሰጠ ነው። • ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 01/2019 • "በተቋማት መካከል የተጠናከረ ግንኙነት እንዲኖር እሰራለሁ" የአማራ ክልል የመንግስታት ግንኙነትና ከክልሉ ውጭ ያሉ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ኮሚሽን • የኮሚሽኑ የ5 ዓመት ስትራቴጂና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ የውይይት መድረክ ተካሄደ • የኮሚሽኑ ራዕይ፣ ተልዕኮ እና ስትራቴጂያዊ ጉዳዮች፣አላማዎችና ግቦች • የኮሚሽነሩ መልዕክት • በኮሚሽኑ ስትራቴጂካዊ ጉዳዮችና ከባለሙያዎች በሚጠበቁ ሙያዊ ሃላፊነቶች ላይ ያተኮረ የኢንዳክሽን ስልጠና ተሰጠ • በክልሉ መንግሥት አዲሱ የግዥ አዋጅና አፈጻጸም መመሪያ ላይ ለስራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ተጠናቀቀ • ኮሚሽኑ ከኢንዱስትሪ ፕሮጀክቶች አገልግሎት ከፍተኛ አመራሮች ጋር በትብብር መሥራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ መከረ • በአዲሱ የክልሉ የመንግሥት ግዥ አዋጅና የአፈጻጸም መመሪያ ላይ ለስራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ስልጠና እየተሰጠ ነው። • ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 01/2019 • "በተቋማት መካከል የተጠናከረ ግንኙነት እንዲኖር እሰራለሁ" የአማራ ክልል የመንግስታት ግንኙነትና ከክልሉ ውጭ ያሉ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ኮሚሽን • የኮሚሽኑ የ5 ዓመት ስትራቴጂና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ የውይይት መድረክ ተካሄደ • የኮሚሽኑ ራዕይ፣ ተልዕኮ እና ስትራቴጂያዊ ጉዳዮች፣አላማዎችና ግቦች • የኮሚሽነሩ መልዕክት
ማስታወቂያ / የጨረታ ማስታወቂያ

ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 01/2019

November 3, 2026

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የመንግስታት ግንኙነት እና ከክልሉ ውጭ ያሉ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ኮሚሽን ልዩ ልዩ ቋሚ የቢሮ ኤሌክትሮኒክስ ፈርኒቸር እቃዎችን፣ አላቂ የቢሮ ዕቃዎችና የጽዳት እቃዎችን እና የተሸከርካሪ የቅባትና መለዋወጫ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊዉ ድርጅት መግዛት ይፈልጋል። ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ።

1.  በዘርፉ አግባብነት ያለዉ እና በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣

2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ያላቸው።

3. የግዥ መጠኑ ብር 500,000.00 (አምስት መቶ ሺህ ብር ) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት ተመዝጋቢ መሆናቸዉን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣

4. በግብር አመቱ ተገቢውን ታክስ እና የግብር ግዴታ የተወጡ መሆኑን የሚያሳይ የታክስ ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ፣

5. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተ.ቁ. 1 እስከ 4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡

6. ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 10 /አስር ቀናት/ ቀን ከቀኑ 11፡30 ድረስ አራት ኪሎ በሚገኘው አልማ ህንፃ (የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ጀርባ የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ከሚገኝበት ህንጻ) ሁለተኛ ፎቅ የአብክመ የመንግስታት ግንኙነትና ከክልሉ ውጭ ያሉ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ኮሚሽን የግዥ፣ፋይናንስ እና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ክፍል ቢሮ ቁጥር 218 በመምጣት ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 / ሁለት መቶ ብር / ብቻ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን በመግዛት መወዳደር ይቻላል፡፡

7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በመሙላት የቴክኒክ እና የፋይናስ ለሚያስፈልጋቸው የቴክኒክ እና የፋይናንስ ሰነዶችን ኦርጅናል እና ኮፒ ሰነዶችን በጥንቃቄ በፖስታ ለየብቻ በማሸግ የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም፣ ፊርማና አድራሻ በትክክል በመሙላት በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን እስከ 11ኛው ቀን ከጧቱ 4፡00 ሰአት ድረስ ማስገባት አለባቸዉ፡፡ 

8. ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጧቱ 4፡00 ሰአት ተዘግቶ በእለቱ ከጧቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል፡፡ 11ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የስራ ቀን ከጧቱ 4፡00 ሰአት ተዘግቶ ከጧቱ 4፡3ዐ ሰዓት ይከፈታል፡፡

9. የጨረታ ማስከበሪያ የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ 1% በባንክ የተመሰከረለት ስፒኦ፣ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ሲፒኦውን ከጨረታው የፋይናንስ ሰነድ ፖስታ ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

10. መ/ቤቱ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

11. የሚፈለጉት ዕቃዎች ዓይነት፣ ብዛትና ስፔስፍኬሽን እንዲሁም የውል ቃሎች ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተዘጋጅቶ የቀረበ መሆኑን እንገልፃለን፡፡ 

ማሣሠቢያ፡- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251-111-26-53-87 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡ 

የአብክመ የመንግስታት ግንኙነት እና ከክልሉ ውጭ ያሉ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ኮሚሽን   

አዲስ አበባ

ተጨማሪ ዜናዎችን ያንብቡ

ማህበራዊ - ሚዲያ

የአማራ የመንግስታት ግንኙነት ዘገባዎችን በሁሉም ማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች ይከታተሉ